የመሪው መልዕክት
እንኳን ወደ ዳሎቻ ወረዳ ይፋዊ ድረ-ገጽ በደህና መጡ። ይህ መድረክ የወረዳችንን ልማት፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እና የወደፊት እቅዶች ለህዝባችን ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው። የብልፅግና ጉዞአችን የሰው ኃይልን፣ የተፈጥሮ ሀብትን እና ማህበራዊ ካፒታልን በዘመናዊ እውቀት እና ቴክኖሎጂ የምናሳድግበት መሰረታዊ የለውጥ ሂደት ነው።
የዳሎቻ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ሪድዋን ሞሶሮ፦ የወረዳ አስተዳደር በመንግሥት አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ለህዝብ ቅርብ የሆነ የአስተዳደር እርከን ሲሆን፣ የህዝብን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ዘላቂ ልማትን፣ መልካም አስተዳደርን፣ የህግ የበላይነትን እና ፍትሃዊ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማረጋገጥ ይሰራል።
የዳሎቻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መልእክት፦ ዛሬ የምንገኝበት ዓለም በዲጂታል እውቀት ፍጥነት የሚመራ በመሆኑ ለዳሎቻ ወረዳ እድገት የሳይንስና ቴክኖሎጂን አቅም መገንባት፣ የዲጂታል ክህሎትን በወረዳችን ማዳበር እንዲሁም አሰራሮችን ወደ ዲጂታል መለወጥ የፓርቲያችን ወሳኝ የትግል አጀንዳ ነው።
ሰብሪ ስሩር (ዳሎቻ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሀላፊ)፦ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን የዘመናዊ ልማት መሠረቶች ሲሆኑ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂም የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን፣ የዜጎችን ተሳትፎ ለማጠናከር፣ የወጣቶችን አቅም ለማሳደግ እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና ያበረክታሉ።